Revive I-5
Seattle
ወደ ሰሜን አቅጣጫ I-5 ከ Martin Luther King Jr. መንገድ እስከ NE Ravenna Blvd
በ2018 ስፕሪንግ እና ሰመር ወቅት፣ የዋሽንግተን ግዛት የትራንስፖርት መምሪያ በኮንትራት የተቀጠሩ 13 ሰራተኞች ወደ ሰሜን አቅጣጫ I-5 በ Martin Luther King Jr. መንገድ እና Northeast Ravenna Boulevard መካከል ያለን 13 ማይል የሚጠጋ መንገድ ይጠግናሉ።
ሥራው የሚከተሉትን ያካትታል፦
የመንገድ መዘጋቶች
አብዛኛው ሥራ የሚከናወነው በሌሊት ነው፣ ነገር ግን ይህ ሥራ ለሁለት የቅዳሜና ዕሁዶች ወደ ሰሜን አቅጣጫ I-5 ከዌስት ሲያትል ብሪጅ እስከ ያስለር ዌይ ድረስ መዘጋት ይፈልጋል። በተጨማሪም፣ ሁለት ረድፎች ብቻ ለትራፊክ ክፍት የሚሆኑባቸው አራት ቅዳሜና ዕሁዶች ይኖራሉ።
በስድስቱ የቅዳሜና ዕሁድ ሥራዎች፣ ሰራተኞች ዓርብ ሌሊት መንገዱን መዝጋት ይጀምራሉ፣ ከዚያም ለሰኞ ጥዋት ጉዞ ሥራቸውን ያጠናቅቃሉ። ሥራው እንደ አየሩ ሁኔታ የሚሰራ በመሆኑ መንገዶች የሚዘጉባቸው ቀናት ወደ ሌላ ሊዘዋወሩ ይችላሉ።
በሳምንት መጨረሻ የሚዘጉበት የጊዜ ሰሌዳ፦
ቀድመው ያቅዱ
ክልል አቀፍ ከፍተኛ መዘግየት ይጠብቁ። WSDOT በግንባታው ወቅት ክልላዊ የትራፊክ ፍሰቱ እንዲቀጥል ለማስቻል የእርስዎን እርዳታ ይፈልጋል።
እባክዎ የሚከተሉትን የጉዞ ምክሮች ልብ ይበሉ፦
ይህን ሥራ ለምን እንሰራለን
I-5 ዋና የትራንስፖርት መስመር ሲሆን ከ50 ዓመት በላይ ሆኖታል። ይህ ሥራ በየዕለቱ ለሚጠቀሙበት ተጓጓዦች እና ጭነት አጓጓዦች አስተማማኝነቱ እንደቀጠለ እንዲቆይ ያግዛል።
የፕሮጀክት መረጃ፦
www.wsdot.wa.gov/Projects/I5/MLKtoRavennaPaveRepair
REVIVE I-5 መረጃ፦
www.reviveI5.com
የኢሜይል ዝማኔዎች፦
https://public.govdelivery.com/accounts/WADOT/subscriber/new
ተጠሪ፦
ቶም ፒርስ
ግንኙነት
206-440-4696
PearceT@wsdot.wa.gov